Food Security, Resilience & WATSAN
In this sector, the Ethiopian Catholic Church Social and Development Commission Coordination Office of Soddo is actively engaged in various initiatives aimed at enhancing the livelihood resilience of underserved communities. Additionally, the office manages several integrated livelihood projects.Currently, the coordination office oversees 10 distinct livelihood projects, supported by a total budget of 1,124,529,252.82 ETB. These projects are designed to directly benefit 89,830 households, comprising 38,514 male and 51,316 female beneficiaries.
በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በሶዶ ሀገረ ስብከት ማህበራዊና ልማት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በወላይታ ዞን አባላ አባያ ወረዳ
በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በሶዶ ሀገረ ስብከት ማህበራዊና ልማት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በወላይታ ዞን አባላ አባያ ወረዳ አባያ ጮካሬ ቀበሌ በቀን 7-10-2024 እ.አ.አ የሀገረ ስብከቱ ጻጻስ ክቡር አቡነ ደጀኔ ሂዶቶ እና የልማት ጽ/ቤቱ ዳይሬክተር አቶ ሙሉነህ ተሰፋዬ፤ የወረዳዉ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት የአከባቢዉ ህዘብ፤የዘርፉ ባለሙያዎችና ኃላፊዎች፤ የሀገር ሽማግሌዎችና የየኃይማኖት መሪዎች በተገኙበት ከካሪታሰ ቼክ እና ከቼክ መንግስት በተገኛ የገንዘብ ድጋፍ የተሠራዉን ንፁ የመጠጥ ዉሃ አሰመርቆ ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጥ ክፍት አድርገዋል፡፡
በተጨማሪም የአከባቢውን ህዝብ ፍላጎት መነሻ ያደረገ የመጠጥ ዉሃን ተደራሽ ለማድረግና አገልግሎት የማይሰጡ ነባር የዉሃ መስመሮች ሥራን ዉጤታማ ለማድረግ ከህዝብና ከመንግስት ጋር የሚሰራዉ ሥራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንንም ክቡር አቡነ ደጀኔ ሂዶቶ አስረድተው የማህበረሰቡን ጥያቄን ለመፍታት ከዘርፉ ባለሙያዎች ጋር መስክ ምልከታና በአከባቢ የሚሰራዉን የአከባቢ ጥበቃ ፕሮጀክት ያለበት ደረጃ ከወረዳ ዋና አሰተዳዳሪ፤ የፓርቲ ጽ/ቤት፤ ግብርና ልማት ጽ/ቤትና ከዉሃዉ ሴክተር ጋር ዉይይት በማድረግና በቦታዉ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም በማድረግ በአከባቢ የሚሰሩ ሎሎች የካቶሊክ ልማት ጽ/ቤት ፕሮጀክት ዉጤታማነትን ለማስቀጠልና አዳደስ ፕሮጀክቶችን ለማስጀመር ከተለያዩ እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ጋር የሚደረገዉ ቅንጅት ከመቼዉም ጊዜ በላይ ርብርብ እንደሚጠይቅ ተናግረዋል፡፡
አያይዘዉም ለሥራዉ ስከት የራሳቸዉን አሻራ ከጅምር ጀምሮ ለሳረፉ ለመንግስትና ለፓርቲ አመራሮች፤ ለባለሙያዎችና ለህዝብ ትልቅ አክብሮታቸዉንና ፍቅራቸዉን ገልፀዋል፡፡